አዲስ ዘመን እሁድ መጋቢት 7 ቀን 2017ዓ.ም
የጨረታ ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር የመ/ስ/ድ/አስ/ባስ/ግልጽ ጨረታ 002/2017
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለስልጣን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን
እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ስለሆነም፦
ሎት 1 --------- አላቂ የቢሮ እቃዎች
ሎት 2-------- ቋሚ የቢሮ እቃዎች የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጀር እና ኤሌክትሮኒክስ አቴንዳንስ መቆጣጠሪያ
ሎት 3 ----------የተሽከርካሪ ቴፕ ፤መረጋገጫ እና ሌሎችም
ሎት 4 ------------ የፅዳት እቃዎች
ሎት 5-------- ፈርኒቸር
ሎት 6--------- የተፈጥሮ አበባ ከነማስቀመጫው
-ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡
-የተጫራቾች በፋይናንስ ቢሮ ዌብሳይት ላይ በአቅራቢዎች ሊስት ላይ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡
-ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በ CPO ማስያዝ አለባቸው፡፡
ሎት 1 ብር 10,000.00 / አስር ሺህ ብር/
ሎት 2 ብር 20,000.00 / ሃያ ሺህ ብር/
ሎት 3 ብር 2,000.00 / ሁለት ሺህ ብር/
ሎት 4 ብር 1,000.00 / አንድ ሺህ ብር/
ሎት 5 ብር 2,000.00 / ሁለት ሺህ ብር/
ሎት 6-------ብር 2,000.00 / ሁለት ሺህ ብር/
-ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ ሆነው ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉና መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ያላቸው መሆን አለባቸው::
-የጨረታ አሸናፊ አሸናፊነቱን ሲገለፅለት ያሸነፈበትን ከጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በCPO
ማስያዝ አለባቸው፡፡
-ተጫራቾች ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ፒያሳ ከሚገኘው
ዋስትና የንግድ ማእከል ህንፃ 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 8/03 የግዥና ንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ
ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ድረስ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
-ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ዋናውን እና ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ የጨረታ ማስታወቂያ
ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው የስራ ቀን ጠዋት 4፡00 ሰአት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
-ጨረታው የሚዘጋበት ቀን የጨረታ ማስታወቂያ በወጣ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ታሽጐ
በዚሁ ቀን ጠዋት 4፡15 ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም በሌሉበት በመ/ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ 4ኛ
ፎቅ ይከፈታል፡፡
-መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ይሁን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
-ዘግይቶ የመጣ የጨረታ ፖስታ ተቀባይነት የለውም ፡፡
-ተጫራቾች ናሙና ለተጠየቀባቸው እቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
አድራሻ፡- ፒያሳ ከሚገኘው ዋስትና የንግድ ማዕከል ህንፃ 8ኛ ፎቅ የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
ቢሮ
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 251111124485
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለስልጣን