አዲስ ዘመን ሰኞ ጥቅምት 17 ቀን 2018 ዓ.ም
የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 06/2018
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጉምሩክ ኮሚሽን የጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ የጽዳት እቃዎች ፣ ልዩልዩ እቃዎች፣ ስፔርፓርት እቃዎች፣ ኮስሞቲክስ ዕቃዎች እና አልባሳት እቃዎች በሐራጅ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ጨቁ 06/2018 ዓ.ም እቃዎቹን ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፡- ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሱ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሱ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
1. በጨረታው ሽያጭ ስርዓት ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የጸና የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ለሀራጅ ጨረታ በጨረታ መክፈቻ ቀን ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
2. ከላይ በተራ ቁጥር አንድ የተገለጸው ቢኖርም ግምታዊ ዋጋው ከብር 500 ሺህ በታች የሆነ ማንኛውም እቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም እንዲሁም የሚሸጠው እቃ ተሽከርካሪ ሲሆን የተሽከርካሪው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተስብ ከሆነ ሰው በስተቀር ማንኛውም እድሜው ከ 18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ ቅድመ ሁኔታዎቹን ማሟላት ሳያስፈልገው በጨረታው ሊሳተፍ ይችላል፡፡
3. በሐራጅ ጨረታ ለወጡት እቃዎች ለመሳተፍ ለአልባሳት ዘርፍ
እቃዎች 20,000 (ሃያ ሺህ ብር)፣ ለልዩ ልዩ ዘርፍ እቃዎች 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) ፣ ለጽዳት ዘርፍ ዕቃዎች እቃዎች 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር)፣ ለእስፔር ፓርት ዘርፍ እቃዎች 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) እና ለኮስሞቲከስ ዘርፍ እቃዎች200,000 (ሁለት መቶ ሺ ብር) ለየብቻው የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ (CPO) በቀጥታ አካውንት ቁጥር 1000296553216 በጋላፊ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስም በማሠራት የጨረታ ሰነዱን እና በተራ ቁጥር አንድ የተገለጹትን መረጃዎች በመያዝ በ
22/02/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡50 ላይ መገኘት አለባቸው፡፡
4. ከላይ በተራ ቁጥር 3 በተገለጸው መሰረት በቂ የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ ተጫራች መወዳደር ወይም መጫረት አይችልም፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-3፡30 ሰዓት የእቃዎቹን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100፡00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ
22/02/2018 ጠዋት 3፡30 ድረስ በውርስ መጋዘን አስተዳደር የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 08 መግዛት ይችላሉ፡፡
6. ለጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎች ለናሙና ዕይታ የሚቀርቡበት ጊዜ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ከጥቅምት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 22 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ከ2፡00-3፡30 ሰዓት የእቃዎቹን ዝርዝር መመልከት ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ የጊዜ ሰሌዳ (ስኬጁል) መሠረት መጫረት ይችላሉ፡፡
|
ተ.ቁ
|
የቅ/ጽ/ቤቱ ስም
|
የጨረታው ኣይነት
|
የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ
|
የጨረታው መዝጊያ እና መከፈቻ ቀንና ሰዓት
|
|
1
|
ጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
|
ሐራጅ ጨረታ
|
እስከ
22/02/2018 ከጠዋቱ
3፡30 ድረስ
|
022/02/2018
3፡50 ሰዓት ይከፈታል
|
የጨረታው መከፈቻ ቦታ፡- በጋላፊ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች በተራ ቁጥር አንድ የተጠቀሱ ማስረጃዎች ኦርጂናል ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
8. ምድብ ለወጣላቸው ሐራጅ እቃዎች ጨረታው የሚካሄደው በምድብ ሲሆን ተጫራቾች አሸናፊ የሚያደርጋቸው ለምድቡ ባቀረቡት የአጠቃላይ እቃዎች ከፍተኛ ዋጋ ይሆናል፡
9. ተጫራቾች ከአሸነፉበት የእቃ ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (15%) የሚጨመር ይሆናል፡፡
10. ተጫራቾች ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በተመለከተ ለአሸናፊው ተጫራች ካሸነፉት የዕቃ ዋጋ ላይ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ውጤቱ በተገለጸ በ3 (ሶስት) ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
11. አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎቹን ባሉበት ሁኔታ የመረከብ እና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይችላል፡፡
12. አሸናፊ ተጫራች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ05 (በአምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን እቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ያለበት ሲሆን ይህን ባይፈጽም ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለመስሪያቤቱ ገቢ ተደርጎ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ የሚቀርብ ሲሆን ነገር ግን አሸናፊው የአሸነፈበትን የእቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ እቃውን ያላነሳ እንደሆነ ለሚቆይበት ተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ የሚከፍል ይሆናል፡፡ ሆኖም እቃውን በሁለት ወር ውስጥ ካላወጣ ለንብረቱ የተከፈለው ዋጋ ለመስሪያቤቱ ገቢ ሆኖ እቃው እንደተተወ ተቆጥሮ በሽያጭ ይወገዳል፡፡
13. በጨረታ የሚሸጠው እቃ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ከመወረሱ በፊት የእቃው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም፡፡
14.ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ውርስ መጋዘን አስተዳደር የሥራ ሂደት ስልክ ቁጥር 033-559-0114 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በጉምሩክ ኮሚሽን የጋላፊ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት