አዲስ ዘመን ረቡዕ የካቲት 04 ቀን
2018 ዓ.ም
የሀራጅ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 20/2018
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጉምሩክ ኮሚሽን የጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ ልዩልዩ ዘርፍ እቃዎች፣ የጽዳት ዘርፍ እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ ዘርፍ እቃዎች፣ ጌጣጌጥ ዘርፍ እቃዎች እና ኮስሞቲክስ ዘርፍ ዕቃዎች በሀራጅ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር 20/2018 ዓ.ም እቃዎቹን ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም፡- ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
1. በጨረታው ሽያጭ ስርዓት ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የጸና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ ያለበት ሲሆን በሀራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ከላይ የተጠየቁትን መረጃዎች በጨረታ መክፈቻ ቀን ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
2. ከላይ በተራ ቁጥር አንድ የተገለጸው ቢኖርም ግምታዊ ዋጋው ከብር 500 ሺህ በታች የሆነ ማንኛውም እቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም። እንዲሁም የሚሸጠው እቃ ተሽከርካሪ ሲሆን የተሽከርካሪው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ ከሆነ ሰው በስተቀር ማንኛውም እድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ ቅድመ ሁኔታዎቹን ማሟላት ሳያስፈልገው በጨረታው ሊሳተፍ ይችላል።
3. በሀራጅ ጨረታ ለወጡት እቃዎች ለመሳተፍ ለልዩልዩ ዘርፍ እቃዎች ብር 44,796 (አርባ አራት ሺ ሰባት መቶ ዘጠና ስድስት ብር) ፣ ለጽዳት ዘርፍ እቃዎች ብር 102,332
(አንድ መቶ ሁለት ሺህ ሶስት መቶ ሰላሳ ሁለት ብር፣ ለኤሌክትሮኒክስ ዘርፍ እቃዎች ብር 20,623 (ሃያ ሺህ ስድስት መቶ ሃያ ሶስት ብር) ፣ ለጌጣጌጥ ዘርፍ እቃዎች ብር 1,502 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ሁለት ብር) እና ለኮስሞቲክስ ዘርፍ ዕቃዎች ብር 502,165 (አምስት መቶ ሁለት ሺህ አንድ መቶ ስልሳ አምስት ብር) ለየብቻው የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ (CPO) በቀጥታ አካውንት ቁጥር 1000296553216 በጋላፊ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስም በማሰራት የጨረታ ሰነዱን እና በተራ ቁጥር አንድ የተገለጹትን መረጃዎች በመያዝ በቀን
10/06/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡40 ላይ መገኘት አለባቸው፡፡
4. ከላይ በተራ ቁጥር 3 በተገለጸው መሰረት በቂ የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ ተጫራች መወዳደር ወይም መጫረት አይችልም።
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከሰኞ እስከ አርብ ዘወትር በስራ ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት የእቃዎቹን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100፡00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10/06/2018 ጠዋት 3፡30 ድረስ በውርስ መጋዘን አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 08 መግዛት ይችላሉ፡፡
6. ለጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎች ለናሙና ዕይታ የሚቀርቡበት ጊዜ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት የካቲት 4/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ የካቲት 10/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ ከሰኞ እስከ አርብ በስራ ሰዓት እና ቅዳሜ ከ2፡00 - 6፡00 ሰዓት የእቃዎቹን ዝርዝር መመልከት ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ የጊዜ ሰሌዳ (ስኬጁል) መሠረት መጫረት ይችላሉ።
|
ተ.ቁ
|
የቅ/ጽ/ቤቱ ስም
|
የጨረታው አይነት
|
የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ
|
የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀንና ሰዓት
|
|
1
|
ጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
|
ሀራጅ ጨረታ
|
እስከ
10/06/2018 ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ
|
በ10/06
2018ዓ.ም ከጠዋት 3፡40 ሰዓት ይከፈታል
|
8. የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡- በጋላፊ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል። ተጫራቾች በተራ ቁጥር አንድ የተጠቀሱ ማስረጃዎች ኦርጅናል ይዘውመቅረብ አለባቸው፡፡
9. ምድብ ለወጣላቸው ሀራጅ እቃዎች ጨረታው የሚካሄደው በምድብ ሲሆን ተጫራቾች አሸናፊ የሚያደርጋቸው ለምድቡ ባቀረቡት የእያንዳንዱ እቃዎች ዋጋ ድምር ከፍተኛው ዋጋ ይሆናል። በተጨማሪም ተጫራቾች በምድቡ ለቀረቡት ለእያንዳንዱ እቃዎች ዋጋ መስጠት አለባቸው።
10. ተጫራቾች ከአሸነፉበት የእቃ ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (15%) የሚጨመር ይሆናል።
11. ተጫራቾች ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በተመለከተ ለአሸናፊው ተጫራች ካሸነፉት የዕቃ ዋጋ ላይ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ውጤቱ በተገለጸ በ3 (ሶስት) ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
12. አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎቹን ባሉበት ሁኔታ የመረከብ እና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይችላል።
13. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ05 (በአምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን እቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ያለበት ሲሆን ይህን ባይፈጽም ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ተደርጎ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ የሚቀርብ ሲሆን ነገር ግን አሸናፊው የአሸነፈበትን የእቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ እቃውን ያላነሳ እንደሆነ ለሚቆይበት ተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ የሚከፍል ይሆናል። ሆኖም እቃውን በሁለት ወር ውስጥ ካላወጣ ለንብረቱ የተከፈለው ዋጋ ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ሆኖ እቃው እንደተተወ ተቆጥሮ በሽያጭ ይወገዳል።
14. በጨረታ የሚሸጠው እቃ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ከመወረሱ በፊት የእቃው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም።
15. ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ ውርስ መጋዘን አስተዳደር የስራ ሂደት ስልክ ቁጥር: 0335590114 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በጉምሩክ ኮሚሽን የጋላፊ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት