አዲስ ዘመን ሰኞ ጥቅምት 17 ቀን 2018 ዓ.ም
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችን በጨረታ ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ሰነድ
የጨረታ ቁጥር፡- PPS/NVP-4FBI/03/02/2018
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ንብረትነታቸው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር፣ የጉምሩከ ኮሚሽን፣ የአማኑኤል የአእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የሆኑ የተለያዩ ብረታ ብረቶችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመስከቱትን መስፈርቶች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
1. በጨረታው ላይ የሚወዳደሩት በማዕድን ሚኒስቴር የተለዩ የብረት አቅላጭ የግል ድርጅቶች የሆኑና የጨረታውን ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ እና መታወቂያ ማቅረብ የሚችሉ ናቸው።
2. ተጫራቾች 6 ኪሎ በሚገኘው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የመንግሥት ግዥ አገልግሎት ግዥና ፋይናንስ ስራ አስፈጻሚ ቢሮ በመምጣት የብረቶቹን ዝርዝር መረጃ፣ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመንግሥት ግዥ አገልግሎት የንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000003785018 ላይ በቴሌ ብር እና ሲቢኢ ብርን በመጠቀም የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከገዙ በኋላ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከ3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ብረታ ብረቶቹን ከላይ በተጠቀሱት መ/ቤቶች በአካል በመሄድ መመልከት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ቁርጥራጭ የብረት ዓይነት የጨረታ መነሻ ጠቅላላ ዋጋውን 2% (ሁለት በመቶ) ዋስትና ያላስያዘ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከጨረታው ሳጥን መዝጊያ ሰዓት በፊትማስገባት አለባቸው።
5. የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል።
6. የጨረታው መገምገሚያ መስፈርት ዋጋ፣ የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ (CPO) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ይሆናል። ይሁንና የብረታ ብረቶቹን ጠቅላላ ግምታዊ ዋጋ 2% (ሁለት በመቶ) ዋስትና ያላስያዘ እንዲሁም በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል።
7. የጨረታ ማስገቢያ ሳጥኑ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመንግሥት ግዥ አገልግሎት መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። ነገር ግን የመክፈቻ ቀኑ የስራ ቀንላይ ካልሆነ (ቅዳሜ ወይም እሁድ ላይ ከዋለ) ወይም በዓል ቀን ላይ ከዋለ ቀጥሎ ባለው የሥራቀን ላይ ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስቀረውም፡፡
8. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ7 (ሰባት) የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 (አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል። ይሁንና ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ተወርሶ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።
9. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ብረታ ብረቶች ሙሉ ክፍያ ከፍለው እስከሚወስዱ ድረስ ለውል አተገባበር ዋስትና የሚሆን የጠቅላላ ዋጋውን 10% (አስር በመቶ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ አለባቸው።
10. ተጫራቾች ያሸነፉትን ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች በራሳቸው ወጪ በማጓጓዝ የሚዛንና ሌሎች ወጪዎችን በመሸፈን ብረታ ብረቱ ከሚገኝበት ስፍራ ቅርብ በሆነ ፕሪንት አውት ማውጣት በሚችል የመንግስት የምድር ሚዛን በማስመዘን ውል በፈረሙ በo የስራ ቀናት ውስጥ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቱን በማንሳት ማጠናቀቅ አለባቸው።
11. ግምታዊ መጠኑ ከፕሪንት አውት ከሚገኘው ትክክለኛ የብረቱ መጠን ጋር የሚኖረው ልዩነት ታስቦ አሸናፊው ተጫራች ተጨማሪ ክፍያ የሚኖርበት ከሆነ የውል ጊዜው ከመጠናቀቁ በፊት ልዩነት የሚኖረውን ሂሳብ መክፈል ያለበት ሲሆን በትርፍነት የሰጠው ተመላሽ የሚደረግለት ገንዘብ ካለም በአገልግሎቱ ተመላሽ የሚደረግ ይሆናል።
12. አገልግሎቱ ያወጣውን የጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከውድድሩ ውድቅ ይደረጋል።
13. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ንብረቶቹን በ10 (አስር) ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡
14. አገልግሎቱ የተሻለ አማራጭ ወይም ሌላ ጨረታውን ለመሰረዝ የሚያበቃ ምክንያት ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡-የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የመንግሥት ግዥ አገልገሎት 6 ኪሎ የካቲት 12 ሰማዕታት ሐውልት አደባባይ ፊት ለፊት
ለበለጠ መረጃ የተቋማችንን ድረ-ገጽ፡- www.pps.gov.et ይጎብኙ
የፌዴራል መንግስት ግዥ አገልግሎት