አዲስ ዘመን ረቡዕ ሚያዚያ 22 ቀን 2017ዓ.ም
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- ግልፅ 02/2017
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ በሎት በተለያዩ
በሎት 1 - አላቂ የቢሮ ጽሕፈት መሣሪያዎችን እና
በሎት 2 - የመኪና ጥገና በጋራጅ የእጅ ዋጋ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በመስኩ ከተሰማሩ ነጋዴዎች ማሠራት
ወይም ዕቃዎችን ለመግዛትና ለማሠራት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት ለመወዳደር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች ሁሉ የሚከተሉትን የጨረታ መወዳደሪያ መስፈርቶች በሟሟላት
መሣተፍ ይችላሉ፡፡
1. ከላይ በተጠቀሱት ለመወዳደር በየዘርፍ ሥራዎች የተሰማሩ፤ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር
የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
2. በገቢዎች ሚኒስቴር በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የተጨማሪ
እሴት ታክስ ከፋይ ስለመሆናቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ፤
3. ተጫራቾች ለሎት 1 ለአላቂ ቢሮ ጽ/መሣሪያ ግዥ ጨረታ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000 (አምስት ሺህ
ብር) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ የተረጋገጠ ጋራንቲ ወይም ሲፒኦ /CPO/ ማስያዝ አለባቸው፡፡
4. ለሎት 2 የመኪና ጥገና በጋራጅ ለእጅ ዋጋ ጨረታ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር)
በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ የተረጋገጠ ጋራንቲ ወይም ሲፒኦ /CPO/ ማስያዝ አለባቸው፡፡
5. አሸናፊ ተጫራች ውሉን ሲፈርሙ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ አለባቸው፡፡
6. ለተሽከርካሪ ጥገና ሀዋሳ ካሉት ጋራዦች ብቻ መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እና መ/ል/ የትራንስፖርት ቢሮ
የሰጣቸውን ብቃት ማረጋገጫ ደረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
7. ተጫራቾች ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሠነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት
ተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት
ልማት ቢሮ ቁጥር 23 ግ/ፋ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ቀርቦ የጨረታ ሠነዱን የንግድ ፈቃዳቸውን በማሳየት 100 / መቶ ብር/ ብቻ በዚህ
አካውንት ቁጥር 1000340576997 በማስግባት መግዛት ይችላሉ፡፡
8. ተጫራቾች የመጫረቻ ሠነዳቸውን ኦሪጂናል ኮፒ ኤንቨሎፕ ውስጥ በሰም በማሸግ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት
አለባቸው፡፡ የጨረታ ሳጥኑም ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት በ15 /አስራ አምስት/ የሥራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ይታሸጋል፡፡
9. ተጫራቾች የሎት 2 (ሁለት) ወይም የመኪና ጥገና በጋራጅ የእጅ ዋጋ ቴክኒካሉና ፋይናንሻሉን በተለያዩ
ኤንቨሎፕ ከታሸገ በኋላ በአንድ ፖስታ ውስጥ በማድረግ ማሸግ አለባቸው፡፡ በዕለቱ የሎት 2 ቴክኒካሉ ክፍል ብቻ ይከፈታል፡፡
10. የጨረታ ሳጥኑም ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት በ16ኛው አስራ ስድስተኛው የሥራ ቀን በ4፡00
ሰዓት ላይ ይታሸጋል፡፡
11. ይህ ጨረታ ከተሞላበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ዋጋ የሚፀናበትን ከ45 ቀናት በታች የጊዜ ገደብ መስጠት
የለበትም፡፡
12. ጨረታው በአስራ ስድስተኛው የሥራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም
ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ግዥ/ፋ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ቢሮ ጨረታውን
የሚከፍት መሆኑን ይገልጻል፡፡ 16ኛው ቀን ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው በሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው
ሰዓት ይከፈታል፡፡
13. አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ከሶስት ቀን በኋላ ባሉት በ5 ቀናት ውስጥ ቀርቦ
ውሉን መፈረም ይኖርበታል፡፡
14. አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈባቸውን ዕቃዎችን ውል ከገባበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ቀናት በራሱ የማጓጓዣ
ወጪ ቢሮ ድረስ በማቅረብ በተፈለገው ወይም በተጠየቀው ስፔስፊኬሽን መሆኑን በባለሙያ ከተጣራ በኋላ ማስረከብ አለበት፡፡
15. አቅራቢው የውል ግዴታውን ሙሉ በሙሉ እንዳጠናቀቀ ክፍያው ወዲያውኑ በቼክ ይከፈለዋል፡፡
16. አቅራቢው የውል ግዴታውን ሙሉ በሙሉ አለመፈፀሙ ሲረጋገጥ በውል ግዴታው መሰረት በሕግ አግባብ ይቀጣል፡፡
17. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ የገዥ ፋይናንስና ንብረት ዳይሬክቶሬት
የስልክ ቁፕር፡- 046-220-00-72
የሲዳማ ብሔራዊ ክስላዊ መንግሥት ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ