አዲስ ዘመን እሁድ ጥቅምት 16 ቀን 2018ዓ.ም
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 5 /2018
ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥስት የሰሜን ሸዋ ዞን የአንጐለላና ጠራ ወረዳ ገንዘብ
ጽ/ቤት
1ኛ በመደበኛ ካፒታል በጀት በተለያዩ ቀበሌ አዲስ የንፁህ መጠጥ ውሃ ግንባታ በምንጭ ማጎልበት በረዘርቫዬርና
በቧንቧ መስመር መዘርጋት ሥራዎች ላይ የውሃ ግንባታ ባለሙያዎችን ወይም የውሃ ግንባታ ተወዳዳሪዎችን አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
2ኛ በወረዳ ውስጥ ከጨኪ- አዳዲ- ሩክስ መንገድ ጥገና እና ከጠንገጎ ገነት ማሪያም መንገድ ሥራ ፕሮጀክት
ኤክስካቫተር 330 HP ለ270 ሰዓት አካፋ ፤ዶዘር ለ50ሰዓት ሩሎ 16 ቶን እና ከዚያ በላይ ለ140 ሰዓት፤ ግሬደር 140 HP
ለ220 ሰዓት፤ ዳምፕ ትራክ ትራክ 723 ግልበጣ ከ0-6ኪ.ሜ ፤ሻወር ትራክ ለ20ቀ 10000 ሊትር እና ከዚያ በላይ የመያዝ አቅም ያለው ሆነው ከገልባጭና ከሻወር
ትራክ ውጭ የሆኑ ማሽነሪዎች ሞዴላቸው 2012 እና ከዚያ በላይ ሞዴል የሆኑ የግንባታ ማሽነሪ ኪራይ በጨረታ በማውጣት ተጫራቾችን
አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል ፡፡
ስለሆነም በጨረታው መካፈል የምትፈልጉ-
1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር
/TIN No/ያላቸውና ከብር 200000 /ሁለት መቶ ሺህ/ ብር በላይ ዋጋ ባላቸው ግዥዎች የሚሳተፋ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ
ቫት ከፋይነት የተመዘገበ እና ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
2. በውሃ ሥራዎች ላይ ፍቃድ ያለው ወይም የአርትዥያን ፍቃድ ያለው
3. በውሃ ነክ ሥራዎች ላይ የአርትዥያን የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የወሰደ ግለሰብ /መሃበሩ መወዳደር ይችላል፡
4. ግንባታውን በውለታው ጊዜ ውስጥ በአይነት በመጠን በጥራት ሳያጓድል መገንባት የሚችል፡፡
5. ማሽነሪዎቹን ከአንድ ሳይት ሌላኛው ሳይት በራሱ ለማጓጓዝ ወይም ለማድረስ ፈቃደኛ የሆነ
6. ማሽነሪዎቹን ወደ ሳይት ሲገቡ ጽ/ቤት በሚፈለገው ቅደም ተከተል ለማስገባት ፍቃደኛ የሆነ
7. ማነኛውንም አይነት የሥራ ልዩነት ካለ ማስተካከያ ይደረግበታል
8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሞልተው ስማቸውን አድራሻቸውን በመጻፍ እና በመፈረም የድርጅቱን ማህተም በማድረግ
ዋና እና ኮፒውን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ ለማሽን ኪራይ 120,000 ለውሃ ግንባታ ሥራ 20,000 በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ
ወይም በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የሚሰጥ በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም ገ/ጽ/ቤት በመሂ1
ያስያዙበትን ደረሰኝ ከኦርጅናል ዋጋ ማቅረቢያ ውስጥ መያያዝ አለበት፡፡ የተጫራቾችን ስምና አድራሻ ፊርማ እንዲሁም የውሃ ግንባታውን
አይነት እና የማሽን ኪራይ በመጥቀስ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 22ኛ ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ በጽ/ቤቱ
በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
9. ጨረታው በዚሁ እለት በ22ኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ይታሸግና በእለቱ ከቀኑ 8:30 ሰዓት ላይ
ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም
10. 22ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልዋለ ጨረታው በሚቀጥለው በመንግሥት የሥራ ቀን ይከፈታል፤
11. አሸናፍው አካል ጥራት ባለው የውሃ ግንባታ ባለሙያ እና የግንባታ ቁሳቁስ መጠቀምና መገንባት አለበት
12. አሸናፍው አካል ሙሉ የፋብርካ ዕቃዎችን እና ሌሎችን ለግንባታ አስፈላጊ እቃዎችን አቅርቦ መሥራት
አለበት።፡
13. የቁፋሮ ሥራ የድንጋይ አቅርቦትና የህ/ሰብ ተሳትፎ ሥራዎች በህ/ሰቡ የሚሸፈን ይሆናል ፡፡
14. አሸናፍው አካል ህ/ሰብን አሳትፎ የሚሠራና ከህ/ሰቡ ጋር ተግባብቶ የሚሠራ መሆን አለበት
15. ተጫራቾች የአንድ ግንባታ የጨረታ ዋጋ የቀረበ ውል ዝርዝር በማድረግ ጠቅላላ ዋጋ ማስቀመጥ ይኖርበታል።
16. በማንኛውም ግንባታ ከብር 20,000/ሃያ ሺህ/ በላይ ለሚሆኑ ግዥዎች አቅራቢው ከሚፈጸምለት ክፍያ
ላይ 3% ቅድመ ግብር ተቀንሶ የሚቀር ይሆናል፡፡
17. ተጫራቾች የእቃውን አይነትም ሆነ መጠን በጨረታው በሙሉ ወይንም በከፊል መሳተፍ ይችላሉ ሆኖም አንድ
ተጫራች በአንድ ሎት ውስጥ ከተዘረዘሩት አይነቶች መካከል ከፋፍሎ መጫረት አይችሉም፡፡
18. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውንም አይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት፡፡
19. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበት ግንባታ በጨረታ ሰነድ ላይ በተገለጸው የሥራ ዝርዝር መሰረት በውሉ መሰረት
ሠርቶ ማስረከብ ይጠበቅበታል፡፡
20. ተጫራቾች ከአንድ ጨረታ በላይ የሚወዳደሩ ከሆነ የሚያሲዙት የጨረታ ማስከበሪያ በተናጠል ወይንም በየሎቱ
ለየብቻው ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
21. የጨረታ ሰነዱን በአን/ጠ/ወ/ገ/ጽ/ቤት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሚከፈትበት ቀን
ድረስ በመንግሥት የሥራ ሰአት ለእያንዳነዱ ሰነድ የማይመለስ 200 ብር መግዛት ይችላሉ፡፡
22. በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ላይ ያልተገለፀ በተጫራቾች መመሪያ እና በኦርጅናል ሰነዱ ላይ በዝርዝር ስለሚገለጽ
ዝርዝራቸውን በትኩረት ማየት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ተጫራቾች በሞሉት ዋጋ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ማድረግና በፍሉድ መደለዝ አይፈቀድም
23. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
24. ጽ/ቤቱ የሚገኘው ከአ/አበባ በስተ ሰሜን 110 ኪ/ሜ ርቀት ደ/ሃርህን መስመር ላይ ነው።
25. ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-6 32-01-47 ወይም 011-6 32-03-04 ደውለው ይጠይቁ።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሰሜን ሸዋ ዞን የአንጐለላና ጠራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት