አዲስ ዘመን ረቡዕ መጋቢት 23 ቀን 2018 ዓ.ም
ብሄራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኽምራ ዞን የሠቆጣ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ለወረዳው በ2018 ዓ.ም በጀት አመት ከዚህ በታች የተገለጸውን ከተራ ቁጥር 1 እስከ ተራ ቁጥር 6 ድረስ ያሉ ግንባታዎችና አቅርቦቶች በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡
ስሆነም
1. የተለያዩ ቀበሌዎች የምንጭ ማጎልበት ጥገና ለማሰራት ሁሉንም ደረጃ ያካትታል
2. በ012 ቀበሌ የድልድይ ዲዛይን በማሰራት የመንገድና ድልድይ ፈቃድ ደረጃ 3 እና ከዚያ በላይ ያለው መሳተፍ ይችላል፡፡
3. ባለ 4 ወለል ህንጻ ግንባታ ህንፃ ተቋራጭ /BC/ ከሆነ ደረጃ 4 እና ከዚያ በላይ ያለው መሳተፍ ይችላል በጠቅላላ ስራ ተቋራጭ/GC/ ከሆነ ደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ ያለው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
4. ኤሌክትሮኒክስ
5. ፈርኒቸር
6. ህትመት
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
1. ተጫራቾች በዘርፋ የ2018 ዓ/ም ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው ያሳደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN/ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3. የግዥ መጠናቸው ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር / እና በላይ ከሆነ የተጨማረ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይ ለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4.ተጫራቾች ጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. የግንባታውም ሆነ የአቅርቦቱ አይነትና ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
6. ተጫራቾች በተራ ቁጥር 1፤2፤4፤5፤6 ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 50.00 /ሃምሳ ብር በተራ ቁጥር 3 ለተገለጸው የህንጻ ግንባታ ለአንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 500/አምስት መቶ ብር/በመክፈል ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከገንዘብ ቤት መግዛት ይችላሉ፡፡
7. የግንባታው ጨረታ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ21 /ሃያ አንድ ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ይቆያል፡፡
8.ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የግንባታም ሆነ አቅርቦት ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የከፍያ ትእዛዝ/ CPO / ወይም በሰቆጣ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በመ/ሂ-ገቢ አድርጎ ኮፒውን ከዋናው የጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፣፣
9. ማንኛውም ተጫራቾች የውሃ ግንባታ የጨረታ ሀሳቡን በአንድ በታሸገ ፖስታ የህንጻ ግንባታ እና የድልድይ ዲዛይን ስራ ፋይናሻሉን እና ቴክኒካል መረጃዎችን በተለያየ ፖስታ በማሸግ በግዥ/ን/አስ/ር ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት የእቃ ግዥ ከ 23/07/2018 እስከ 7/08/2018 ዓ/ም ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በተጨማሪም በጨረታ ሰነዱ ላይ ስማቸው፣ፌርማቸውን፣ ሙሉ አድራሻ፣ የድርጅቱ ማህተም መሟላት ያለባቸው ሲሆንጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ8/8/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ በ4፡00 ሰዓት ግዥ /ን/ስስ/ር ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 ይከፈታል፡፡
ግንባታና ዲዛይን ስራን ከ23/7/2018 እስከ 13/08/2018 ዓ/ም ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን፣ በተጨማሪም በጨረታ ሰነዱ ላይ ስማቸው ፊርማቸውን፣ ሙሉ አድራሻ፣ የድርጅቱ ማህተም መሟላት ያለባቸው ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቀን14/08/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ በ4፡00 ሰዓት ግዥ /ን/አስ/ር ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 ይከፈታል፡፡
10.ተጫራቾች አሽናፊነታቸው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀን ውስጥ የዋጋውን 10% በባንክ በተረጋገጠ CPO/ወይም በጥሬ ገንዘብ መሂ- በማስያዝ ውል መፈረም አለባቸው፡፡
11.ተጫራቾች አሽናፊነታቸው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ አስይዘው ውል ካልፈረሙ መ/ቤቱ የጨረታ ማስከበሪያውን የመውረስ መብት አለው፡፡
12. መ/ቤቱ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 ለቀረቡት የጨረታ ሰነድ ማንኛውም ህጋዊ ተወዳዳሪ የሚወዳደርባቸውን የጨረታ ሰነዶች በጨረታ ሰነዱ ላይ የቀረቡት የግንባታ አይነትና የግዥ ሁኔታ ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን/ መሰረት የመሙላት ግዴታ አለበት፣፣
13 አሸናፊው የአሸነፈውን ግንባታ ከሚፈለግበት ቦታ ሰርቶ የማስረከብና ግዥውን በሚፈለግበት ሴክተር መ/ቤት በማስረከብ ሂሳቡን በስሙ የማወራረድ ግዴታ አለበት፡፡
14. በጨረታው ቅሬታ ያላቸው ተጫራቾቸ ጨረታው ከተከፈተና አሸናፊው ከተለየ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ባለው ቅሬታቸውን ለሚመለከታቸው አካል ማቅረብ አለባቸው፣ ከተጠቀሰው ቀን በኋላ የሚቀርብ አቤቱታ ተቀባይነት የለውም፣
15. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 5 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0334400416 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
16. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
17. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፣
18. የጨረታው መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኽምራ መስተዳድር ዞን የሠቆጣ
ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት