አዲስ ዘመን ማክሰኞ ሚያዝያ 21 ቀን 2017 ዓ.ም
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በሀዋሳ ከተማ አስ/ የአካባቢ ጥበቃ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ጽ/ቤት ለሚያሰራው ሥራ የሚያስፈልጉ ለአጥር የሚሆን ሽቦና አንግል አይረን እና ለጋቢዮን መስሪያ የሚሆን ደረጃውን የጠበቀ ድንጋይ ግዥዎችን ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ያስፈለገ በመሆኑ በዘርፉ ሕጋዊ ፈቃድ ካላቸውን ድርጅት/ማህበር መካከል በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሠረት:-
1) ለአጥር የሚሆን ሽቦና አንግል አይረን ሎት
01/2017
2) ለጋቢዮን መስሪያ የሚሆን ደረጃውን የጠበቀ ድንጋይ
02/2017 ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች/ማህበር መወዳደር ይችላሉ፡-
1. በዘርፉ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው፤
2. በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፣
3.ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፣
4. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው ፣
5. የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ (አዲሱ ከተማ አስተዳደር ህንፃ ) አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 ( ሃምሳ አራት) በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 /ሃያ
አንድ/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርባችሁ ሰነድ ብር
200(ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ገዝቶ ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲ ፒ ኦ (CPO ) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት ፡፡
7. ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ ቀናት በፋይ/ኢኮ/ልማ/ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 (ግዢ
ኬዝ ቲም) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
8. ጨረታው በ6ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን በበዓላት ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል፡፡ የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል ፡፡
9. ማንኛውም ተጫራች በሲዳማ ክልል እና ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ተመሳሳይ ሥራ በእጁ ላይ ካለና የሥራው አፈጻጸም 70%
ካልደረሰ በጨረታ መወዳደር አይችልም፡፡ ሥራው 70% እና
በላይ የደረሰ ከሆነ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ማረጋጋጫ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
10. በጨረታ አከፋፈት ስነ-ስርዓት የተነበበው ዋጋ እና በአርትሜቲክ ቼክ በሚደረግበት ግዜ በሁለቱ መካከል ከ2% (ከሁለት ፐርሰንት) በላይ ሆነ በታች ልዩነት ካለ ተጫራቹ በቀጥታ ከጨረታ ውጪ ይደረጋል፡፡
11. ለጨረታ ያስገቡት ዋጋ ከቀረበ የመሐንዲስ ዋጋ ጥናት ጋር ሲነፃፀር ወደ ላይ ከ አሥራ አምስት ፐርሠንት (15%)
በላይ ከሆነ በቀጥታ ከጨረታ ውጪ ይደረጋል፡፡
12. ለጨረታ ያስገቡት ዋጋ ከቀረበ የመሐንዲስ ዋጋ ጥናት ጋር ሲነፃፀር ወደ ታች ከአሥራ አምስት ፐርሠንት (15%) በታች ከሆነ ለእንዳንዱ ሥራ ዝርዝር ተጨባጭ የወቅቱ ገበያ የዋጋ ትንተና (Direct Unite cost Analysis sheet) ማቅረብ የሚችል እና ለዚህም መ/ቤቱ የጠየቀውን የውል ማስከበሪያ ዋስትና ገንዘብ ወይም መያዣ ገንዘብ መጠን ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርበታል፡፡
13. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁፕር
046-220-99 63/046-212-13-34
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና/ኢኮ/ል/መም/ያ