አዲስ ዘመን ረቡዕ ሚያዚያ 22 ቀን 2017ዓ.ም
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ መለያ ቁጥር DDCBO- 10/2017
በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ከ2017 በጀት ዓመት ጀምሮ ለአንድ ዓመት በሚቆይ ውል መሠረት
ለሰራተኞች የሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጡ የሚኒባስ እና የደብል ጋቢና ተሽከርካሪዎችን በኪራይ መልክ ለማሰራት ስለሚፈልግ በዘርፍ
ያሉትን አቅራቢዎች ጋብዞ ለማጫረት ይቻል ዘንድ መ/ቤታችን ያዘጋጀውን ይህን የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ
በማውጣት ተጫራቾችን ካወዳደረ በኋላ በጨረታው አሸናፊ ከሚሆኑት አቅራቢዎች ጋር የስራ ውል ስምምነት በማድረግ ተሽከርካሪዎቹን ለመከራየት
ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው መሣተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም ህጋዊ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡
1) ተጫራቾች አግባብነት ያለው በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው፣የንግድ
ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት፣ የቫት ወይም የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና በጨረታ መወዳደር
የሚያስችል የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ታክስ ክሊራንስ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
2) ተጫራቾች በመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ድረ-ገፅ ላይ በመንግስት የኤሌክትሮኒክስ ግዥ(GP
on- line system) ላይ በአገልግሎት አቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምዝገባ ማስረጃ የምስክር
ወረቀት ማቅረብ ይሆርባቸዋል፡፡
3) የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ማስታወቂያው እና በጨረታ ሰነድ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች
መሠረት ሲሆን በጨረታው የሚወዳደሩት ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
4) ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ግዥ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር )በመክፈል የድሬዳዋ ጉምሩክ
ቅ/ጽ/ቤት በሀብት አስተዳደር ስራ ሂደት ስር ከሚገኘው የግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 002 በአካል በመቅረብ መውሰድ
ይችላሉ፡፡
5) ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና መጠን ብር 5,000.00 ብር (የአምስት ሺህ ብር) ከታወቀ
ባንክ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም በ Certified Payment Order (CPO)፣ በካሽ፣ ቢድ ቦንድ ወይም
በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ድርጅቶች ከሚመለከተው አካል የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ደብዳቤ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ማቅረብ
ይርባቸዋል። ከዚህ ውጪ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ተቀባይነት የለውም፡፡ ተጫራቾች ከባንክ
የሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ቢያንስ ለሰማንያ ስምንት (ለ88) ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል፡፡
6) ተጫራቾች ለጨረታ የሚያቀርቡት የሰራተኞች ሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች ኪራይ አገልግሎት
አቅራቢዎች የተሽከርካሪ ባለንብረትነት ማረጋገጫ ሊብሬ እና የሶስተኛ ወገን የመድህን ዋስትና ሽፋን ማስረጃ ሰርተፍኬቱን ኮፒ አድርገው
ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
7) ተጫራቾች የሰራተኞች ሰርቪስ ተሽከርካሪዎች ኪራይ አገልግሎት ላይ ለመሳተፍ የቀረቡ ከሆነ የጨረታው
አሸናፊው የሚለየው 50% በቴክኒክ ግምገማ እና 50% በፋይናንስ ግምገማ ብቃቱ ተገምግሞ መሠረታዊ መመዘኛዎችን ያሟላና ዝቅተኛ
ዋጋ ያቀረበ መሆኑ ተረጋግጦ አጠቃላይ ድምር ውጤቱ ከፍተኛ ነጥብ ያገኘ ከሆነ በአሸናፊነት ይመረጣል፡፡
8) ተጫራች የሰራተኞች ሰርቪስ ተሽከርካሪዎቹን የቴክኒክ ግምገማ ለማስገምገም ከወዲሁ አስፈላጊውን ቅድመ-
ዝግጅት በማድረግ ከመ/ቤታችን ውጪ ገለልተኛ በሆኑ የቴክኒክ ባለሙያዎች ለማስገምገም ተሽከርካሪዎቹን በአካል ማቅረብ አለባቸው፡፡
9) ተጫራቾች በጨረታው ለሚወዳደሩባቸው ማንኛውም ተሽከርካሪዎች ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለማስረከብ ወደ
መስሪያ ቤታችን ሲመጡ የጨረታ ሰነዱን አዘጋጅተው ማቅረብ ያለባቸው:
ሀ. ፋይናንሻል ዶክመንት ኦርጅናል፤
ለ. ቴክኒካል ዶክመንት ኦርጅናል፤
ሐ. ፋይናንሻል ዶክመንት ኮፒ፣ እና
መ. ቴክኒካል ዶክመንት ኮፒ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
10) ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያቀርቧቸው የጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ በእያንዳንዱ ገፅ ላይ የድርጅቱን
ስም፤ ማህተም፣ ሙሉ አድራሻ እና ፊርማ በማድረግ አሟልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
11) በጨረታ መከፈቻው ቀን ተጫራች ግለሰብን ወይም ድርጅትን በመወከል የሚቀርብ ማንኛውም ሰው ህጋዊ ውክልና
ያለው መሆን ይጠበቅበታል፡፡
12) በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ የሚቀርብ ዋጋ ተቀባይነት የለውም፡፡
13) ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ
- በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ይዘጋል፤
- በዚያኑ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና
ፋይናንስ ቡድን ቢሮ 002 ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻ የመጨረሻው ቀን እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው
የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
14 ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሠረት የመጫረቻ ሰነዳቸውን ማቅረብ አለባቸው፡፡ከጨረታው ደንብና
መመሪያ ውጪ የሚቀርብ ማንኛውም የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
15) ተጫራቾች ተሽከርካሪዎቹን የሚያከራዩበትን ዋጋ ቅ/ጽ/ቤቱ ባዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ከቫት
በፊት ያለውን ዋጋ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው።
16)ለአሸናፊ ተወዳዳሪዎች በጨረታው ማሸነፋቸው እንደተገለፀላቸው ቅሬታ ያላቸው ተወዳዳሪዎች ቅሬታቸውን
በጽሁፍ ለቅ/ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ በ 5 የስራ ቀናት ውስጥ ማቅረብ አለባቸው፡፡በውድድሩ የቀረበ ቅሬታ ከሌለ አሸናፊ ድርጅቶች
በ15 ቀናት ውስጥ በቅ/ጽ/ቤቱ በአካል ቀርበው ግዢውን ከሚፈጽመው አካል ጋር ውል መዋዋል ይጠበቅባቸዋል፡፡
17) በጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ማድረግ፤ በፍለድ ማጥፋት ወይም የጨረታ ዋጋው ሲፃፍ በቁጥሩ ላይ
ደርቦ ወይም አድምቆ መፃፍ ከጨረታ ውድድር ውጪ ያደርጋል፤
18) ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0251115107 ወይም 0251110765 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
አድራሻ፡- ድሬዳዋ ከተማ ሳቢያን ቀበሌ 02 እሸት ግሮሰሪ አካባቢ በሚገኘው የድሮው ይገዙ ሆቴል ህንፃ
ላይ
የድሬዳዋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 002
በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት